አሜሪካ እና አውሮጳ ኅብረት ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ ለመክተት ጥረት እያደረጉ ነው ተባለ

—-
የአሜሪካ እና የአውሮጳ የሰብዓዊነት እና ልማት መሪዎች በመጭው ሳምንት ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ በቀጥታ የሚተላለፍ ውይይት ለማድረግ ማቀዳቸውን ዲቨክስ (Devex) አስነብቧል። ውይይቱ በመጭው የG-7 ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ አጀንዳ ሆና እንድትቀርብ ለማስቻል ለጉዳዩ ትኩረት አልሰጡትም ያሏቸውን አንዳንድ የአውሮጳ አገራት ለማሳመን ያለመ መሆኑ ታውቋል። 
በትናንትና ዕለት አዲስ አበባ የሚገኙ የፈረንሳይ እና የጀርመን ቆንስሎች በትውተር ገጻቸው የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦናል ማለታቸው በG-7 ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን አጀንዳ አድርጎ ለማንሳት ያለውን ውጥን ለማሳካት በማሰብ ሳይሆን እንዳልቀረም ተዘግቧል።

Related posts

ከአውደ ውጊያ ወደ ሙሉ ድል እንዴት እንሸጋገር?

የጎንደር ጉዳይ!

ምርጫ 2013 | ምሉዕነት፣ ታማኝነት እና ግልጸኝነት