ምርጫ ቦርድ እነ እስክንድር ነጋን በእጩነት ሊመዘግብ ነው


አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙትን የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን በዕጩነት የመመዘገብ ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ። ቦርዱ ይህን የገለጸው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 26 ላስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ አንደኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ነው። 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ችሎት ፊት ቀርበው እንደተናገሩት፤ ባልደራስ ፓርቲ ቀደም ሲል አስመዝግቧቸው በነበሩ ዕጩዎች ምትክ፤ ለምርጫ እንዲቀርቡለት የሚፈልጋቸውን ግለሰቦች እንዲያሳውቅ በተቋማቸው በኩል ጥያቄ ቀርቦለታል። በዚህም መሰረት ፓርቲው በትላንትናው ዕለት አዲሶቹን ዕጩዎች ማሳወቁን አስረድተዋል።
ቦርዱ የፓርቲው አመራሮች ለሚወዳደሩባቸው ቦታዎች ቀደም ሲል አሳትሟችው የነበረውን ወደ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጾ በዚህም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጭ ማድረጉን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። 
ፍርድቤት እነ እስክንድር ነጋ በእጩነት እንዲወዳደሩ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔውን ለመተግበር እንደሚቸገር የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፎ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፤ አዲስ ዘይቤ

Related posts

ከአውደ ውጊያ ወደ ሙሉ ድል እንዴት እንሸጋገር?

የጎንደር ጉዳይ!

ምርጫ 2013 | ምሉዕነት፣ ታማኝነት እና ግልጸኝነት