የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማን ጋር ውል እንደተፈራረመ ያውቃሉ?


በዲስ አበባ ከተማ 500ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል የተባለው “Project 2000” ኩባኒያ ትክክለኛ የፋይናንስ ተቋም አመሆኑን የደቡብ አፍሪቃ የዜና አውታር አረጋግጧል።
ይህ ኩባንያ ከአሁን በፊት ሌሴቶ ውስጥ ስቴዲዮም ለማስገንባት 2.4 ቢሊዮን የደቡብ አፍሪቃ ራንዳ (90 ሚሊዮን ዶላር) እንግሊዝ ውስጥ ከሚገኝ የንግድ ልማት ባንክ (Commercial Development Bank) የብድር ማረጋገጫ አግንቻለሁ በማለት ተመሳሳይ ውል ፈርሞ ነበር። ነገር ግን የእንግሊዝ የፋይናንስ ኃላፊዎች እንደማያውቁት እና የተፈቀደለት ስላይደለ አጭበርባሪ (scam) ሊሆን ስለሚችል ከዚህ ተቋም ጋር የንግድ ሥራ እንዳትሰሩ ሲሉ መክረው እንደነበር የደቡብ አፍሪቃው EWN Reporter አስነብቧል።
በሕገ-ወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምን ማረጋገጫ አግኝተው ከዚህ ድርጅት ጋር ለመፈራረም እንደቻሉ የታወቀ ነገር የለም።

Related posts

ከአውደ ውጊያ ወደ ሙሉ ድል እንዴት እንሸጋገር?

የጎንደር ጉዳይ!

ምርጫ 2013 | ምሉዕነት፣ ታማኝነት እና ግልጸኝነት