Policy/ፖሊሲ

by Fasil Abebe

የራስ ሚድያ ፖሊሲና መርሆዎች /Ras Media Policy and procedure 

ሰኔ  8 2013 ሜሪላንድ ዩ. ስ. ኤ./ June 8, 2021 Maryland USA

መግቢያ

የራስ ሚድያ ተገቢ የሆነ አለማቀፍ የመረጃ ልውውጥን  ለአማራ ማህበረሰብ ለማረጋገጥ  እንዲሁም በውጭ ያሉ የተለያዩ የአማራ ማህበራትን ለጋራ ዓላማ ለማስተባበር የተመሰረተ ለትርፍ ያልቆመ የሚድያ ድርጅት ነው። ይህ ሚድያ በተለይ በማንነታቸው ምክንያት ለሚሰደዱ ፣ ለሚገደሉና ለሚሰቃዩ ግፉአን ሁሉ የህሊና ድምጽ ነው። በማንነት ምክንያት የሚደረጉ አስከፊ ጥቃቶችን ከመነሻው ለመከላከል የሚያስችሉ መፍትሄ ሃሳቦችን ማዳበርና የተፈናቀሉ ተጎጂዎችን የሚታደግ ሂደቶች ላይ በማተኮር ይሰራል። ከላይ የተገለጹትን ጉዳዮች በሳተላይት ቲቪ እንዲሁም በማህበራዊ ድረ ገጽ የስርጭት አገልግሎት በማካሄድ ላይ እንገኛለን።በዚህም መሰረት፥

በአማራ ማህበረሰብ ህልውና ላይ የተደቀኑ አሁናዊ ችግሮችን ለመለየትና ለመቅረፍ የሚያግዙ መረጃና ማስረጃ አሰብስቦ በሜድያ ዘዴዎች በማሰራጨት በማሀበረሰቡ ውስጥ የጋራ ተግባቦትና ግንዛቤን ማሳደግ።

ከሃገር ውጭና በሃገር ውስጥ ያሉ የማህበረሰቡ አባላትና ማህበራት እንዲሁም ሌሎች ከላይ የተጠቀሰውን ሁኔታ አሳሳቢነት በመረዳት የአማራ ግፉአንን የሚደግፉ ኢትዮጵያውያንን ማቀራረብና ማያያዝ።

በተለያየ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮች በ አሁኑ ወቅት በሃገር ውስጥ ተፈናቅለው ህይወታቸውን በጉስቁልና ውስጥ ለመምራት የተገደዱ  ቤተሰቦች የአስቸኳይ ጊዜና መልሶ ማቋቋም ድጋፎችን በልዩና ሜድያ አገዝ በሆነ ስልት የተጎጂ ተደራሽነትን ማሻሻልና መከታተል።

የራስ ሚድያ ዋና ዋና ዓላማዎች

፩: በአሁኑ ወቅት በ አማራ ህብረተሰብ ላይ የተደቀኑ የህልውና ስጋቶች እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበረሳባዊ የመሻሻል ጥያቄዎችን ለማስተናገድ በሚያስችል ሁኔታ የሚድያ ፕሮግራሞችን መቅረጽ፥

፪፡ በማንነታቸው ምክንያት የተፈናቀሉ የተጎጂዎችን ሁኔታ  ለርዳታ በሚያመች መንገድ ዘገባዎችን ከአካባቢው በማሰባስብ   የባለድርሻ አካላትን ተገቢ ትኩረት እንዲያደርጉ ያሚያስችል የሚድያ ስልትበመጠቀም ማንቃትና ማትጋት ፥

፫፡ በአካባቢ ደረጃ ተጎጂዎችና ለጋሾችን የሚያቀራረብ ማህበራዊ የትስስር መረብ መዘርጋት እንዲሁም ዕርዳታን ለሚያስቡ የሃገር ውስጥና የውጭ ሀገር ማህበረሰብ አባላት የችግሩን ጥልቀት በሚመጥን ሁኔታ እንዲረዱ  የሚያስችል ፕሮግራም በሳተላይት ለብዙሃን መገናኛ አገልግሎት ያውላል።

የራስ ሚድያ ዝርዝር የስራ አቅጣጫ

I ፡ መደበኛ የሳተላይት ሚድያ አገልግሎት ስርጭት ማካሄድ:

፩፡ ዜናዎችና ሰበር ዜናዎች

1- ዕለታዊና ሰበር ዜናዎችን ከላይ የተጠቀሰውን የሜድያ ዋነኛ ዓላማዎች በሚያማክልና ቅድሚያ በሚሰጥ የዜና አደረጃጀት ማዘጋጀትና ማቅረብ፥

2 – የዜና ቅደም ተከተልን የአማራ ማህበረሰብ  ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱና የሚያሳስቡ ዜናዎች የቅድሚያ ሽፋንና በዋና ዜናነት ለመጠበቅ የሚያስችል አሰራርን ያወጣል።

3 – ሌሎች ማናቸውንም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የሚድያ ድርጅቶች  ዜናዎች ዋቢ አድርጎ ለማቅረብ ወይንም ለማስተጋባት ይልቅ  ይህንን የሚመዝን አማራጭ የውጭ ዘናዎች ወይንም ነጻ አቀራረብ ያላቸው የግል ሚድያዎች አስተያየቶችን ወይንም ዜናዎችን  ማካተትና የገደል ማሚቶ አይነት የዜና አቅርቦትን በተቻለ መጠን ማስቀረት።

4 – የዜና ሽፋን ይዘትን በየዕለቱ ሰማያ በሃያ በሆነ (የኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ) (ከማህበራዊና መዝናኛና አለም ዓቀፋዊ ዜና) የዘገባ ንጽጽር እንዲዘጋጅ ጥረት ማድረግ።

5 – የዘናን ይዘት ሚዛናዊነት ተአማኒነትና ስነምግባራዊነት የሚቀንሱ የድምጽ የምስል ወይንም የፖለቲካ ፓርቲ ወገናዊነት አቀራረብ በመራቅ የሚድያውን ስምና ዝና መጠበቅ።

6 – የዜና ምንጮች የፌደራልና የክልል መስሪያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ቡድኖችና አካላት ተጠሪዎችየዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የህዝባዊ ድርጅቶች ተጠሪዎች አንዲሁም የተፎካካሪ ፓርቲዎችና የውጭና የሃገር ውስጥ የዜናና መገናኛ ተቋሞች ናቸው።

፪፡ የውይይትና ትንታኔ መድረክ

ሀ) በሚድያው አማካሪ ድጋፍ ሰጪ ግብረሃይል የሚቀመጡ አቅጣጫዎችን በመመርኮዝ የራስ ሚድያ አድማጭ ተመልካችን ማህበራዊ ግንዛቤን ለማሳደግ በሚያስችል አቀራረብ የውይይትና ትንታኔ መድረክ ያዘጋጃል። ይህንንም ለማከናወን ከሁለት እስከ አራት የሚደርሱና ለትንታኔ ውይይት ብቁ የሆኑ መደበኛ የሚድያው አንቂዎች መድቦ በሳምንት ከሁለት እስከ አራት  ቀናት የሳተላይት  ስርጭት ይካሄዳል።

ለ) የሰቶች የወጣቶችና የመሳሰሉት ንኡስ ማህበረሰባዊ ዝግጅቶችን  ለዚህ በተመደበ አወያይ የሚድያው ባለሙያ አማካኝነት የሚቀርብ ሳምንታዊ ፕሮግራም ይቀርባል። በዚህም መሰረት ለአንድ ጊዜ ወይንም ለተካታታይ ጥቂት ዝግጅቶች  የሚቀርብ በነጠላ ወይንም ከሁለት እስከ አራት በማይበልጡ ተጋባዥ ተወያዮች  የሚካሄድ ዝግጅት ይቀርባል።

፫፡ የመልካም አስተዳደር ጥንቅር ዘገባ( Documentary on Good Governance)

በዚህ የጥንቅር ዘገባ   የሚቀናበር ዝግጅት በተለይ ተገቢ ባልሆነ የፖለቲካ ወይንም የኢኮኖሚ ትጽዕኖዎች የተጎዱ ግለሰቦችና ቤተሰቦችን በማነጋገር ችግራቸውን ለሚመልለከተው ሁሉ በማሳወቅና በመጠየቅ አጋዝ ማህበራዊ ግፊት የመፍጠር ትልዕኮ ይኖረዋል። በሳምንት ሁለት ቀናት በሚቀርበው ብበዚህ ዝግጅት  

1 – በማንነታቸው ምክን ያት ለረጅም ጊዘ ከሚኖሩብበት መንደር የተፈናቀሉ ሰዎችን፥

2 – በፖለቲካ አመለክካከታቸው ምክንያት ከስራ ከንግድ ተግባራቸው የተገፉ  የላግባብ የታሰረ ሰው ቤተሰቦችን

3 – በዘር ማጽዳት እንቅስቃሴ አካላቸውን ወይንም ቤተሰባቸውን ያጡ ፥ 

4 – በምዝበራና በሙስና ችግሮች ምክኛት ሃብትና ንብረታቸውን ያጡ ግለሰቦችና 

5 – የሚመለከታቸውን የመንግስት ተወካዮች የእንባ ጠባቂና ስብዓዊ መብት ጥበቃ ተጠሪዎችና ባለስልጣናት በማነጋገር ዘን አዘጋጅቶ ጥንቅር ዘገባ ያቀርባል።

፬፡ የአማራ ግፉአን የረድዔት ሰንሰለት ክትትል ዘገባ ( Displaced Amaras RAS media matching & monitoring)

በማንነታቸው ምክን ያት ከመደበኛ ህይወታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያው ለሚጉላሉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች የአስቸኳይ እርዳታና የምመልሶ ማቋቋም ተግባር የተደራሽነት ማጠናከሪያ  መደበኛ የሚድያ ክትትል( ) ማድረግ።

ይህንንም ለመፈጸም

፩፡ በ አለም ዙሪያ ግፉአን ተኮር ድጋፍ ሰጪ የ አ ካባቢ ቻፕተሮችን ማደራጀት

፪፡ የ አስቸኳይ እርዳታንና መልሶ ማቋቋም ዕገዛን ለሚሹ ተፈናቃይ ወገኖች የድጋፍ መከታተያ የሚድያ ድረገጽና ሰብዓዊ ሰንሰለት ይዘረጋል፥

፫፡ ይህንንና ከላይ የተዘረዘሩ የሚድያው ዓላማዎችን ከወቅታዊ የሃገሪቱ ሁኔታ ጋር በማመሳከር በየሁለት ሳምንቱ ተሰብስቦ የሚድያውን ስራ አቅጣጫ የሚያስይዝ የአማካሪዎች ግብረሃይል ይኖረዋል።

፭: የማህበራዊ ድረገጽ ስርጭት፥

የራስ ሚድያ  ከላይ እንደተቀመጠው የተቋቋመበትን አላማ ይዘት በመከተል በሚዘረጋው ማህበራዊ ድረገጽ አማካኝነት በየዕለቱ  ደጋፊና ተመጋጋቢ የሚድያ ውጤት ስርጭትን ያካሂዳል። ይህንንንእነዚህም

፩፡ ፌስ ቡክ (Facebook),  ፪፡ ዩ ቱዩብ (YouTube) ,፫፡ ትዊተርና (Twitter) , ፬፡ ኢንስቲግራም (Instagram) ናቸው።

ለማካሄድ የማህበራዊ ሚድያ ግብረሃይል በማዋቀርና የዚህን ዘርፍ የሚመራ ተጠሪ ባለሙያን ቀጥሮ ያሰራል። 

፮፡ የባህልና መዝናኛ ዝግጅት ዘገባና ጥንቅር

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘገባዎች ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን ከዤና ይልቅ በጥንቅር መልክ ተዘጋጅተው ይቀርባሉ፣

1- አንድነትን ተስፋን የሚያንጸባርቁ የጋራ ማህበራዊ በዓሎችና ወጎችን አከባበር ዘገባ ፥

2 – ለኢትዮጵያ የፊተኛ ዘመን ፥ድገት ጉልሕ አስተውጽ ኦ ላደርጉ ግለሰቦች መታሰቢያና መዘከሪያ ዘገባ፥

3 – በአሁኑ ዘመን በኪነ ጥበብ በስፖርት በትምህርት በቴክኒዮሎጂ የላቀ አፈጽጸም ያላቸውን ለማክበር የሚዘጋጅ ዘገባ ናቸው።የራስ ሚድያ በማንነታቸው ምክንያት በመተከል አጣየና ወለጋ አካባቢዎች

(ከዚህ ሰነድ ጋር የተያያዘውንየራስ ሚድያ ቁጥር 006 ክት ትል የቅጾችን ናሙና በቀጣይ አፕዴቶት ይጫናሉ )