ከአውደ ውጊያ ወደ ሙሉ ድል እንዴት እንሸጋገር?

by Baye Teshager

በሳምንታው የምኩራብ ፕሮግራማችን የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተነስተዋል

“ጦርነቱ ገና አላለቀም። ጦርነቱ አለቀ የሚባለው ወያኔ ከአማራ ክልል ተጠራርጎ ሲወጣና … አጠቃላይ የወታደር መዋቅሩ ፈርሶ በሲቪል አስተዳደር ሲተካ ነው” ~ እያሱ ኤፍሬም

ድሉ ዘላቂ እንዲሆን ምን መደረግ አለበት?

1/ ወደ ትግራይ ተሂዶ የህወሓትና የኦነግ አመራሮች ወደ ሕግ መቅረብ አለባቸው2/ ገለልተኛ የሆነ ጠንካራ ኮሚሽን መቋቋም አለበት … የተፈናቀሉ ወደ ቤታቸው ካልተመለሱ፣ የፈረሱ ካልተገነቡ ድሉ ድል አይሆንም3/ በጦርነት ዘላቂ መፍትሔ አይመጣም። … ከትግራይ ማኅበረሰብ ጋር ያሉ ልዩነቶች፣ ቅራኔዎችና አለመስማማቶች ቁጭ ተብሎ በውይይት መፍታት ያስፈልጋል ~ ግርማ ካሳ

ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ እነማን ናቸው?

የቅድሚያ ቅስሚያ መሰጠት ያለበት ለእናቶችና ለእህቶቻችን ነው። የአካላዊ ጥቃት ሕመሞች በቤተሰብ ላይ፣ በግለሰብ ላይ ትልቅ ቁስል የሚጥሉ ናቸው። ~ እያሱ ኤፍሬም

መልሶ ለማቋቋም ሪሶርስ ከየት ይገኛል?

ዲያስፖራውን የስፖንሰርሽፕ ስራ እንዲሰራ በማድረግ፤ ከምዕራባዊያን ጋር ያለንን ግንኙነት በማሳሻል ዕርዳታ የሚገኝበትን መንገድ መፈለግና በተለይ ከአሜሪካ ጋር ያለውን መካረር ማርገብ ያስፈልጋል፤ መንግሥት አንዳንድ በጀቶችን በማጠፍ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ማዛወር አለበት ~ ግርማ ካሳ

You may also like