የእነእስክንድር ነጋ የመመረጥ መብት ተረጋገጠ

by RAS Media


በሕግ ጥላ ስር የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አባላት የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ፣ ወ/ሮ አስቴር ስዮም እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል የመመረጥ መብታቸው ሊከብርላቸው እንደሚገባ የፌደራል ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ (National Electoral Board of Ethiopia- NEBE -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ) ከሕግ አግባብ ውጭ እነእስክንድር ለምርጫ መወዳደር አይችሉም በማለት የመመረጥ መብታቸውን የከለከለ እና ፍርድ ቤት ቀርቦ ተከራክሮ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ እና አስፈላጊ የሆኑ የሕግ አንቀጾችን መርምሮ እነእስክንድር ነጋ ምንም እንኳን በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ቢሆንም የአገሪቱ ሕግ ለምርጫ ከመወዳደር አይከላክላቸውም በማለት የመመረጥ መብታቸውን አረጋግጧል።
በቀጣይ ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያስፈጽም አያስፈጽም ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በአስተያየት መስጫ ሳጥናችን ውስጥ ያገኙታል።

You may also like