ግብጽ እና ሱዳን ከግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የቆየ የምድር፣ የአየር እና የባህር ጦር ልምምድ ማድረጋቸው ታውቋል። የናይል ዘበኞች (Guardians of the Nile) የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የጦር ልምምድ የሁለቱን አገራት የጦር ዝግጁነት ለማደስ የተደረገ እንደነበር ተገልጿል።
የግብጽ ጦር ቃል-አቀባይ ጣሚር ኤል-ራፋኢ በዒላማ ውስጥ የገቡ እና ያልገቡ አካላትን እንዴት መምታት እንደሚቻል የስልጠናው አካል የነበረ መሆኑን ሲገልጡ የሱዳን ጦር ተጠሪ አብዳላህ አልበሽር በበኩላቸው የጦር ልምምዱ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ከምትገነባው ግድብ ጋር የተገናኘ አይደለም ብለዋል።
ግብጽ እና ሱዳን መሰል የጦር ልምምድ ሲያደርጉ ከረጅም ጊዜ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በሦስቱም የጦር አውዶች ማለትም የምድር፣ የአየርና የባህር ኃይልን ያጠቃለለ መሆኑ በቀጠናው ያለው ውጥረት ወደ ሌላ መልክ እንዳያመራ እንደሚያሰጋ እየተነገረ ይገኛል።
previous post